On Amazon.it: https://www.amazon.it/Complete-Concordances-James-Bible-Azzur/dp/B0F1V2T1GJ/


Wikipedia - የመንግሥት ሃይማኖት

የመንግሥት ሃይማኖት

ከWikipedia

ዛሬ በዓለሙ የሚገኙት መንግሥታዊ ሃይማኖቶች።
ዛሬ በዓለሙ የሚገኙት መንግሥታዊ ሃይማኖቶች።

የመንግሥት ሃይማኖት በአንድ መንግሥት ዘንድ የተመሠረተ ሃይማኖት ወይም ይፋዊ እምነት ነው። ይህ ሲባል ግን የተመሠረተው ሃይማኖት መሪዎች የመንግሥቱ መሪዎች አይደሉም፤ እንደዚህ ከሆነ ግን ያው መንግስት «Theocracy» ይባል ነበር። 'የተመሠረተው ሃይማኖት' ማለት በመንግሥት የተደገፈው እምነት ወይም ትምህርት የሚመለከት ነው።

ይዞታ

[ለማስተካከል] አይነቶች

መንግሥት ሃይማኖቱን እስከ ምን ደረጃ ድረስ እንደሚደግፈው በየአገሩ ይለያያል። ከቃል ድገፋ ብቻ እስከ ገንዘባዊ እርዳታ ድረስ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ አገር ውስጥ የሌሎቹ ሃይማኖቶች ተከታዮች ነጻነት ቢያገኙም በሌላ አገር በኩል ግን ሌላ ሃይማኖት ሁሉ ይከለከላል። ወይም ተከታዮቹ ይሳድዳሉ።

በአውሮፓ ውስጥ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት (ወይም ጸረ ማርያም የተባሉት) አብያተ ክርስትያናት በ16ኛ ክፍለ ዘመን ሲወዳደሩና ሲተጋገሉ፤ መንግሥታት የመሪዎቻቸውን ምርጫ ተከተሉ፤ ይህም መርኅ በአውግስቡርግ ውል (1547 ዓ.ም.) ጸደቀ። የእንግሊዝ ንጉሥ በ1525 ዓ.ም. የፕሮቴስታንት እምነት ስለ አጸደቀ፤ በፓፓ ፈንታ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ላይኛ መሪ እሱ ሆነ። በስኮትላንድ ግን በመቃወም የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ሆነ።

አንዳንዴ፣ አንድ አገር ወይም ክፍለሀገር ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች በገንዘብ ይደግፋል። ለምሳሌ በፈረንሳይ ውስጥ በአልሳስ-ሞዘል ጠቅላይ-ግዛት እንዲሁም በጀርመን አገር እንዲህ ይደረጋል።

በአንዳንድ ኮሙኒስት አገር በተለይ በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፤ መንግስት አንዳንድ ሃይማኖት ድርጅት ብቻ ይፈቀዳልና ሌሎቹ አይፈቀዱም። እንደነዚህ ባሉት አገሮች የተመረጠው ትምህርት ወይም እምነት የማርክስ ወይም የማው ጸ-ቱንግ ጽሑፎች ይሆናል።

[ለማስተካከል] ከመመሠረት መነቀል (Disestablishment)

ከመመሠረት መነቀል (Disestablishment) ማለት አንድ ሃይማኖት ወይም ቤተ ክርስቲያን የመንግስት አካል ከመሆን የሚቋረጥበት ሂደት ነው። ለምሳሌ በእንግሊዝ አገር በመጨረሻ 19ኛ ክፍለ ዘመን እንዲህ ለማድረግ የታገለ እንቅስቃሴ ቢኖርም አልተከናወነምና መቸም አልሆነም። በአይርላንድ ግን የአይርላንድ ቤተ ክርስቲያን በ1863 ዓ.ም. ከመመሠረት ተነቀለ። በ1912 ዓ.ም. ደግሞ በዌልስ ውስጥ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ከመመሠረት ተነቀለ።

አሜሪካ ሕገ መንግሥት (1ኛ የሕግ መለወጫ፣ 1783 ዓ.ም.) መሠረት ምንም ሃይማኖት እንዳይመሠረት በግልጽ ይከለከላል። ከዚህም ጋር መንግስት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጥልቅ ከማለት ይከለከላል። ሆኖም የተወሰነ ክፍላገር መንግሥት የተመሠረተ ሃይማኖት ከመኖር አይከለክልም። ለምሳሌ ኮነቲከት እስከ 1810 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው፤ ማሳቹሰትስም እስከ 1825 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው።

ዛሬ የአሜሪካ ክፍላገሮች ሁሉ ለኗሪዎቻቸው የሃይማኖት ነጻነት ያረጋግጣሉ። ከነዚህም መካከል 8ቱ እነሱም አርካንሳው፣ ሜሪላንድ፣ ማሳቹሰትስ፣ ስሜን ካሮላይና፣ ፔንስልቬኒያ፣ ደቡብ ካሮላይና፣ ተነሲና ቴክሳስ፤ እምነተ ቢስ ሰው ከመሾም ቢከለክሉም ይህ አይነት ሕግ ግን አሁን (ከ1953 ዓ.ም. ጀምሮ) ተግባራዊ ሆኖ አይቆጠረም።

[ለማስተካከል] ክርስቲያን አገሮች

የሚከተሉት መንግስታት የክርስትና ቤተ ክርስቲያን ዓይነት በየአይነቱ መሠርተዋል።

[ለማስተካከል] ሮማ ካቶሊክ

እነዚህ አገራት ወይም ክፍላገራት የሮማ ካቶሊክ ሃይማኖት በይፋ አላችው።


*(ከተሐድሶ እና ከጥንታዊ ካቶሊክ ጋር)
**(ከተሐድሶ ጋር)

[ለማስተካከል] ምስራቅ ኦርቶዶክስ

እነዚህ መንግሥታት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይነት በይፋ አሏቸው።

  • ቆጵሮስ (የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን)
  • ግሪክ (የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን)
  • ሞልዶቫ
  • ፊንላንድ (የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን)*

*(ከሉተራን ጋር)

[ለማስተካከል] ሉተራን

እነዚህ መንግሥታት የሉተራን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።


*(ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ ጋር)

[ለማስተካከል] አንግሊካን

ይህ መንግሥት የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አለው።

[ለማስተካከል] ተሐድሶ (ሪፎርምድ)

እነዚህ መንግሥታት የተሐድሶ ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።

  • ስዊስ አገር እነዚህ ክፍላገራት (የስዊስ ተሐድሶ ቤተክርስቲያን) ፦
    • አርጋው*
    • ባዘልቤት*
    • በርን*
    • ግላሩስ**
    • ግራውቢውንደን**
    • ሽቪውጽ**
    • ቶርጋው**
    • ኡሪ**
    • ጹሪክ
  • ስኮትላንድ - የስኮትላንድ ቤተክርስቲያን 'አገራዊ ሃይማኖት' ሲሆን ከመንግሥት ሙሉ ነጻነት አለው።

*(ከሮማ ካቶሊክ እና ከጥንታዊ ካቶሊክ ጋር)
**(ከሮማ ካቶሊክ ጋር)

[ለማስተካከል] ጥንታዊ ካቶሊክ

እነዚህ መንግሥታት 'ጥንታዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን' የተባለው አይነት በይፋ አላቸው።

  • ስዊስ አገር እነዚህ ክፍላገራት ('የስዊስ ክርስቲያን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን') ፦
    • አርጋው
    • ባዘልቤት
    • በርን

(በነዚህም 3 ውስጥ የሮማ ካቶሊክና የተሐድሶ አይነቶች አብረው ይፋዊ ናቸው)

[ለማስተካከል] የእስላም አገሮች

የሚከተሉት መንግስታት የእስልምና ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

[ለማስተካከል] የቡዲስት አገሮች

የሚከተሉት መንግስታት የቡዳ ሃይማኖት ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

  • ቡታን ('ድሩክፓ ካግዩ' ቲቤታዊ አይነት)
  • ካምቦዲያ ('ጤራቫዳ' አይነት)
  • ሩስያ ውስጥ የሆነ ክፍላገር፦
    • ካልሙኪያ (ቲቤታዊ አይነት)
  • ስሪ ላንካ (ጤራቫዳ አይነት)
  • ታይላንድ (ጤራቫዳ አይነት)
  • ምየንማ

[ለማስተካከል] ሕንዱ አገራት

ከአገራት ኔፓል ብቻ የሕንዱ ሃይማኖትን በኦፊሴል ይዞ ነበር። በቅርብ ጊዜ ግን፣ በአመጻዎች ችግር ምክንያት ይህ ሁኔታ ተለውጦ እምነቱ ከመመሰረት ተነቀለ።

[ለማስተካከል] አይሁድና

በእስራኤል ሕገጋት መሠረት አገሩ 'የአይሁድ አገር' ይባላል። ይሁንና 'አይሁድ' የሚለው ቃል ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን አንድ ዘር ወይም ወገን ማለት ደግሞ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አይሁድና ምን ማለት እንደሚሆን ለአገሩ ክርክር ሆኗል። አሁን እስራኤል አንዳንድ ተቋም በተለይም የኦርቶዶክስ አይሁድ ተቅዋማት ይደግፋል፤ ከዚህም በላይ የኦርቶዶክስ አይሁድ፣ የእስላም፤ የክርስቲያንና የድሩዝ ችሎቶች ይፈቅዳል።

[ለማስተካከል] በጥንት

[ለማስተካከል] ሱመር

በጥንት ሱመር መንግሥታት የመንግስት ሃይማኖት ጽንሰ ሀሣብ ይታወቅ ነበር። እያንዳንዱ ከተማ-አገር ወይም ሕዝብ የራሱን አማልክት ወይም ጣኦት ይኖሩት ነበር። የድሮ ሱመር አለቆች ብዙ ግዜ ለከተማቸው አምላክ ቄሶች ደግሞ ነበሩ።

[ለማስተካከል] ግሪክ

ሰዎቹ በብዙ አማልክት ቢያምኑም እያንዳንዱ ጥንታዊ ግሪክ ከተማ የገዛ ዐቃቤ አምላኩ ነበረው። እንዲሁም የአቴና አምላክ አቴና ነበረች፤ የስፓርታም አርቴሚስ፣ የዴሎስ አፖሎ፣ የኦሊምፒያ ዜውስ ነበሩ።

[ለማስተካከል] ቻይና

በቻይና የሃን ሥርወ መንግሥት (214 ክ.በ. - 212 ዓ.ም.) የኮንፉክዩስ (ኮንግፉጸ) ሃይማኖት በይፋ ተከተለ። ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር። ይህ ሃይማኖት እስከ 573 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ሆኖ ቀጠለ። ያንጊዜ የቻይና መንግስት ሃይማኖት የቡዳ ሃይማኖት ሆነ። ዳሩ ግን በ10ኛ መቶ ዘመን ውስጥ መንግሥቱ ወደ ኮንፉክዩስ ሃይማኖት ተመለሰ።

[ለማስተካከል] የሮማ ሃይማኖት

በሮማ መንግሥት ላይኛ ቄስ የተባለው ቄሳር ወይም ንጉሡ ነበረ። ብዙ ግዜ ንጉሡ በትእቢቱ ብዛት እኔ አምላክ ነኝ በግልጽ ያዋጅ ነበር። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ ለንጉሡ ካልጸለዩ ይሙት በቃ በሕዝብ ላይ ደረሰባቸው። በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ለሮማ ንጉስ አንጸለይም ብለው ተገደሉ።

በ303 ዓ.ም. ንጉሡ ጋሌሪዎስ አልጋ ላይ ወድቆ ትንሽ ሊያርፍ ሲል በመንግሥቱ ግዛት ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች ሁሉ ይቅርታ ሰጠ። ከዚህ በፊት የክርስትናን ሃይማኖት ለማጥፋት በሙሉ ሞክሮ ነበር። ከዚያ ሁለት የጋርዮሽ ቄሣሮች 1ኛ ቆስጠንጢኖስ እና ሊቂኒዎስ በ305 ዓ.ም. የሚላኖ አዋጅን አወጡ። ይህ ህግ ለሰው ሁሉ የሃይማኖት ነጻነት በማረጋገጥ የክርስቲያኖች መሬት ያለ ገደብ እንዲመልስላቸው የሚያዝዝ ነበር።

በ317 ዓ.ም. ቆስጠንጢኖስ የኒቂያ ጉባኤ ጠሩ። ቢባልም ለብዙ አመታት ከዚህ በኋላ በጥምቀት እንዳልገቡ መገንዘብ ይረዳል። አሁን ክርስትና በሮማ ውስጥ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆን በብዙዎች ሕዝብ በግልጽ ይከተል ጀመር። በዚህ ዘመን አካባቢ ግን የሮማ መንግሥት ጎረቤቶች የነበሩት የአክሱም መንግሥትና አርሜኒያ ከነገስታታቸው ጥምቀት አንስቶ በይፋ ወደ ክርስትና ገብተው ነበር።

ለጥቂት ግዜ ከ353 እስከ 355 ዓ.ም. ድረስ የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ መንግሥቱን ወደ ድሮ አረመኔ እምነት መለሠው። ተከታዩ ግን ክርስቲያን በመሆኑ አገሩን ወደ ክርስትና ፕሮግራም መለሰ።

በመጨረቫ በ372 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉሡ 1ኛ ቴዎዶስዮስ አዋጅ መሠረት የሮማ መንግስት ሃይማኖት በይፋ ተደረገ።

[ለማስተካከል] ፋርስ

የሳሳኒድ መንግሥት (218-643 ዓ.ም.) ይፋዊ ሃይማኖት የዛርጡሽ ሃይማኖት ነበር።

[ለማስተካከል] በአውሮፓ ውስጥ ያሉት መንግሥታት ሃይማኖቶች ወይም ቀድሞ የነበሯቸው ሃይማኖቶች

ሀገር ሃይማኖት አይነት ከመመሰረት የተነቀለበት አመተ ምኅረት
አልባኒያ1 ከነጻነት ጀምሮ የለም
አንዶራ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
አንሃልት (ጀርመን) የአንሃልት ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
አርሜኒያ የአርሜንያ ሃዋርያዊ ቤተክርስቲያን ተዋሕዶ 1913
ኦስትሪያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1910
ባደን (ጀርመን) ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና የባደን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ካቶሊክና ሉተራን 1910
ባየርን (ጀርመን) ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1910
ብሩንዝቪግ-ሊውነቡርግ (ጀርመን) የብሩንዝቪግ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ቡልጋሪያ የቡልጋርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1938
ቆጵሮስ የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ አልተነቀለም
ቼኮስሎቫኪያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1912
ዴንማርክ የዴንማርክ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
እንግሊዝ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን አንግሊካን አልተነቀለም
ኤስቶኒያ የኤስቶኒያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1932
ፊንላንድ2 የፊንላንድ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1911
ፈረንሳይ3 ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1897
ጂዮርጂያ የጂዮርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1913
ግሪክ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ አልተነቀለም
ሄሰ (ጀርመን) የሄሰ እና የናሶ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሀንጋሪ4 ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1840
አይስላንድ የአይስላንድ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
አይርላንድ የአይርላንድ ቤተክርስቲያን አንግሊካን 1863
አየርላንድ ሪፑብሊክ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1965
ጣልያን ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1976
ሊክተንስታይን ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሊፐ (ጀርመን) የሊፐ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ 1910
ሊትዌኒያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1932
ሊውበክ (ጀርመን) ስሜን እልባዊ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሉክሳምቡርግ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ማልታ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሜክለንቡርግ (ጀርመን) የሜክለንቡርግ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሞናኮ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ አልተነቀለም
ሆላንድ የሆላንድ ተሐድሶ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ 1787
ኖርዌ የኖርዌ ቤተክርስቲያን ሉተራን አልተነቀለም
ኦልደንቡርግ (ጀርመን) የኦልደንቡርግ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ፖላንድ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1931
ፖርቱጋል ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1902
ፕሩሲያ (ጀርመን) 13 የጀርመን ወንጌላዊ አብያተ ክርስትያናት ሉተራን 1910
ሮማኒያ የሮማኒያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1939
ሩሲያ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1909
ጦሪንገን (ጀርመን) የጦሪንገን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሳክሰን (ጀርመን) የሳክሰን ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ሻውምቡርግ-ሊፐ (ጀርመን) የሻውምቡርግ-ሊፐ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ስኮትላንድ የስኮትላንድ ቤተክርስቲያን ፕሬስቢቲሪያን አልተነቀለም
ሰርቢያ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ኦርቶዶክስ 1935
እስፓንያ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ 1970
ስዊድን የስዊድን ቤተክርስቲያን ሉተራን ጥር 1992
ቱርክ እስልምና 1920
ቫልደክ (ጀርመን) የሄሰ-ካሰልና የቫልደክ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910
ዌልስ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን አንግሊካን 1910
ቩርተምበርግ (ጀርመን) የቩርተምበርግ ወንጌላዊ ቤተክርስቲያን ሉተራን 1910

^1:  በ1959 ዓ.ም. የአልባኒያ መንግስት በይፋ ከሃዲነት «የመንግስት ሃይማኖት» አደረገና ሃይማኖቶች ሁሉ ከለከለ። ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ቆየ።

^2:  የፊንላንድ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን እስከ 1801 ዓ.ም. ድረስ የስዊድን ቤተክርስቲያን ነበረ። ከ1801 እስከ 1909 ዓ.ም. ድረስ ፊንላንድ የሩስያ ቅኝ አገር ስትሆን የተለየ የፊንላንድ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን በሩሲያ መንግስት በፊንላንድ ተመሰረተ። በ1911 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት መሠረት ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የጋርዮሽ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን ነው።

^3:  በፈረንሳይ ውስጥ በ1793 ዓ.ም. ስምምነት መሠረት የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራንም ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም አይሁድና ሁሉ በመንግሥት የተደገፉ ሆኑ። በ1897 ዓ.ም. መንግሥት ከሃይማኖት ግን ተለየ።

^4:  በሀንጋሪ የ1840 ሕገ መንግሥት መሠረት አምስት የጋርዮሽ አብያተ ክርስቲያናት ተመሰረቱ፤ እነሱም የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስና የዩኒታሪያን ቤተክርስቲያኖች ናቸው። በ1887 ዓ.ም. አይሁድና ስድስተኛ የተምሰረተ እምነት ሆነ። በ1940 ዓ.ም. ግን የሀንጋሪ መንግሥት ሃይማኖቶቹን ሁሉ መለየት ተወ።

Static Wikipedia March 2008 on valeriodistefano.com

aa   ab   af   ak   als   am   an   ang   ar   arc   as   ast   av   ay   az   ba   bar   bat_smg   bcl   be   be_x_old   bg   bh   bi   bm   bn   bo   bpy   br   bs   bug   bxr   ca   cbk_zam   cdo   ce   ceb   ch   cho   chr   chy   co   cr   crh   cs   csb   cv   cy   da   en   eo   es   et   eu   fa   ff   fi   fiu_vro   fj   fo   fr   frp   fur   fy   ga   gd   gl   glk   gn   got   gu   gv   ha   hak   haw   he   hi   ho   hr   hsb   ht   hu   hy   hz   ia   id   ie   ig   ii   ik   ilo   io   is   it   iu   ja   jbo   jv   ka   kab   kg   ki   kj   kk   kl   km   kn   ko   kr   ks   ksh   ku   kv   kw   ky   la   lad   lb   lbe   lg   li   lij   lmo   ln   lo   lt   lv   map_bms   mg   mh   mi   mk   ml   mn   mo   mr   ms   mt   mus   my   mzn   na   nah   nap   nds   nds_nl   ne   new   ng   nl   nn   nov  

Static Wikipedia (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2007 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2006 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu

Static Wikipedia February 2008 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu